La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሠዉ በሕ​ዝቡ ሁሉ ዘንድ የነ​በረ የካ​ህ​ኑ​ንም ሕግ አያ​ው​ቁም ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መሥ​ዋ​ዕት በሠዉ ጊዜ የካ​ህኑ ብላ​ቴና ይመጣ ነበር፤ በእ​ጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበር፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ጊዜ ካህናቱ ከሕዝቡ ጋራ ባላቸው ግንኙነት የሚፈጽሙት ወግ ነበር፤ ይኸውም ማንም ሰው መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለውን ሜንጦ ይዞ ይመጣል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የካህናትም ልማድ በሕዝቡ ዘንድ እንዲህ ነበረ፥ ሰው ሁሉ መሥዋዕት ሲያቀርብ ሥጋው በተቀቀለ ጊዜ የካህኑ አገልጋይ ይመጣ ነበረ፥ በእጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበረ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ካህናቱ ከሕዝቡ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እንደዚህ ነበር፦ ሰው ሁሉ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ሥጋው በመብሰል ላይ እያለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለውን ሜንጦ ይዞ ይቀርብ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የካህናትም ልማድ በሕዝቡ ዘንድ እንዲህ ነበረ፥ ሰው ሁሉ መሥዋዕት ሲያቀርብ ሥጋው በተቀቀለ ጊዜ የካህኑ ሎሌ ይመጣ ነበረ፥ በእጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበረ፥

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 2:13
5 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ካህ​ናቱ ሕዝ​ቡን ለመ​ቀ​ደስ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ እን​ዳ​ይ​ወጡ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​በ​ስ​ሉ​በት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ጋ​ግ​ሩ​በት ስፍራ ይህ ነው።”


ወደ ድስ​ቱም ወይም ወደ ምን​ቸቱ ወይም ወደ አፍ​ላሉ ወይም ወደ ቶፋው ይሰ​ድ​ደው ነበር። ሜን​ጦ​ውም ያወ​ጣ​ውን ሁሉ ካህኑ ለእ​ርሱ ይወ​ስ​ደው ነበር፤ በሴ​ሎም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊሠዉ በሚ​ወጡ በእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ሁሉ ላይ እን​ዲህ ያደ​ርጉ ነበር።


ዔሊም እጅግ አረጀ፤ ልጆ​ቹም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ያደ​ረ​ጓ​ቸ​ውን፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ሴቶ​ችም ጋር እን​ደ​ሚ​ተኙ ሰማ።


በመ​ሥ​ዋ​ዕቴ ላይና በዕ​ጣኔ ላይ ስለ ምን በክፉ ዐይን ተመ​ለ​ከ​ትህ? የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በፊቴ ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ በቀ​ዳ​ም​ያቱ ስለ አከ​በ​ር​ሁህ ከእኔ ይልቅ ልጆ​ች​ህን ለምን መረ​ጥህ?