1 ሳሙኤል 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፦“ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ ከበጎችና ከላሞች መንጋዎች መልካም መልካሙን አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አመጣን፤ የቀሩትንም ፈጽሜ አጠፋሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ “ሰራዊቱ ከአማሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጦቹ በጎችና በሬዎች ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳይገድሉ የተዉአቸው ናቸው፤ የቀሩትን ግን በሙሉ አጥፍተናል” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ “ሠራዊቱ ከአማሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጦቹ በጎችና በሬዎች ለጌታ ለአምላክህ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳይገድሉ የተዉአቸው ናቸው፤ የቀሩትን ግን በሙሉ አጥፍተናል” ብሎ መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም “እነርሱ ወታደሮቼ ከዐማሌቃውያን የማረኩአቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጥ የሆኑትን የቀንድ ከብቶችና በጎች ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ አምጥተዋል፤ የቀሩትን ግን በሙሉ ደምስሰናል” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ መልካሞቹን በጎችና በሬዎች አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አምጥተዋቸዋል፥ የቀሩትንም ፈጽመን አጠፋን አለው። |
ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ “ሂዱ፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ” አላቸው።
ሕዝቡ ግን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር በጌልጌላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችና በሬዎች ከምርኮው ወሰዱ” አለው።
ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ ሁሉ አጋግን፥ ከከብቱና ከበጉ መንጋ መልካም መልካሙን፥ እህሉንም፥ ወይኑንም፥ መልካም የሆነውን ሁሉ አዳኑ። ፈጽመው ሊያጠፉአቸውም አልወደዱም፤ ነገር ግን የተናቀውን ሁሉ ፈጽመው አጠፉት።