1 ሳሙኤል 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሎቷንም በእግዚአብሔር ፊት ባበዛች ጊዜ፥ ካህኑ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐና ባለማቋረጥ ወደ እግዚአብሔር በጸለየች ጊዜ፣ ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጸሎትዋንም ባለማቋረጥ ወደ ጌታ ባቀረበች ጊዜ፥ ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐና በዚህ ዐይነት ጸሎትዋን በማስረዘም ብዙ ጊዜ ስለ ቈየች፥ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጸሎትዋንም በእግዚአብሔር ፊት ባበዛች ጊዜ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር። |
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።