1 ጴጥሮስ 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፥ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሣራም አብርሃምን “ጌታዬ” እያለች ትታዘዘው ነበር፤ እናንተም ምንም ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ የእርሷ ልጆች ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሣራም አብርሃምን “ጌታዬ” እያለች ትታዘዘው ነበር፤ እናንተም ምንም ሳያስፈራችሁ መልካም ብታደርጉ የእርሷ ልጆች ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የታዘዙትም ሣራ አብርሃምን “ጌታዬ!” እያለች ትታዘዝለት እንደ ነበረው ዐይነት ነው፤ እናንተም መልካም የሆነውን ነገር ብታደርጉና አንዳች የሚያስፈራ ነገር ባያስደነግጣችሁ የእርስዋ ልጆች ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፥ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ። |
ሐሰት የተናገርሽው፥ እኔንም ያላሰብሽው፥ በልብሽም ነገሩን ያላኖርሽው ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔም ዝም አልሁሽ፤ አንቺም አልፈራሽኝም።
ጴጥሮስና ዮሐንስም እንዲህ ብለው መለሱላቸው፥ “እግዚአብሔርን ያይደለ እናንተን ልንሰማ በእግዚአብሔር ፊት ይገባልን? እስኪ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።