ወደ ናኮንም አውድማ ደረሱ፤ ዖዛም በሬዎቹ አነቃንቀዋት ነበርና ይይዛት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ታቦት እጁን ዘረጋ፤ አስተካከላትም። ሲይዛትም በሬው ወጋው።
1 ነገሥት 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤተ መንግሥት ሠርቶ ከፈጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያንጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች የአባቶቻቸውን ቤቶች መሳፍንት ንጉሡ ሰሎሞን በጽዮን ሰበሰባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ፣ የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የእስራኤልን ነገድ አለቆችና የእስራኤልን ጐሣዎች ሹማምት ሁሉ፣ ንጉሡ ሰሎሞን ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት ለማምጣት፥ ወደ ቤተ መቅደሱም ለማስገባት፥ የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጐሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን ለማምጣትና ወደ ቤተ መቅደሱ ለማስገባት የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጐሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች የአባቶቻቸውን ቤቶች መሳፍንት፥ ንጉሡ ሰሎሞን ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰባቸው። |
ወደ ናኮንም አውድማ ደረሱ፤ ዖዛም በሬዎቹ አነቃንቀዋት ነበርና ይይዛት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ታቦት እጁን ዘረጋ፤ አስተካከላትም። ሲይዛትም በሬው ወጋው።
ሰሎሞንም ነቃ፤ እነሆም፥ ሕልም ነበረ፤ ተነሥቶም ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ በጽዮንም በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አሳረገ፤ የደኅንነትንም መሥዋዕት አቀረበ፤ ለአገልጋዮቹም ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደረገ።
ዳዊትም፥ የእስራኤልም ሽማግሌዎች፥ የሻለቆችም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት በደስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።
የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰች ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት ሲዘፍንና ሲጫወት አይታ በልብዋ ናቀችው።
ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉና የፍርድ አለቆችን፥ ንጉሡንም በየተራ የሚጠብቁትን አለቆቹን፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሡና በልጆቹ ሀብትና ንብረት ላይ፥ መባ ባለበት ላይ የተሾሙትን ጃንደረቦችንም፥ ኀያላኑንና ሰልፈኞቹን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ፋሲካ ያደርጉ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ ደግሞም ወደ ኤፍሬምና ወደ ምናሴ ደብዳቤዎችን ጻፈ።
ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ልጆች በከተሞቻቸው ሳሉ፥ ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆነውን፥ የተመረጠውን፥ የከበረውንና መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም።
ጽድቄን አመጣኋት፤ ከእኔ ዘንድ የምትገኝ መድኀኒትንም አላዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኀኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
ኢያሱ የእስራኤልን ልጆች ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውንም፥ አለቆቻቸውንም፥ ፈራጆቻቸውንም፥ ሹሞቻቸውንም ጠርቶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ እነሆ ሸምግያለሁ፤ ዘመኔም አልፎአል፤
ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበሰበ፤ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች፥ አለቆቻቸውንም፥ ጸሓፊዎቻቸውንም፥ ፈራጆቻቸውንም ጠራቸው። በእግዚአብሔርም ፊት አቆማቸው።