1 ነገሥት 3:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “ደኅነኛውን ሕፃን ለሁለት ቈርጣችሁ ለአንዲቱ አንዱን ክፍል፥ ለሁለተኛዪቱም ሁለተኛውን ክፍል ስጡ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ንጉሡ፣ “በሉ በሕይወት ያለውን ልጅ ከሁለት ክፈሉና ለአንዷ ግማሹን፣ ለሌላዪቱም ግማሹን ስጡ” ብሎ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሉ እንግዲህ በሕይወት ያለውን ልጅ ለሁለት ቁረጡና ለእያንዳንዷ ሴት ግማሽ አካሉን ስጡ” ሲል አዘዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሉ እንግዲህ በሕይወት ያለውን ልጅ ለሁለት ቊረጡና ለእያንዳንዷ ሴት ግማሽ አካሉን ስጡ” ሲል አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም “ደኅነኛውን ሕፃን ለሁለት ከፍላችሁ ለአንዲቱ አንዱን ክፍል፥ ለሁለተኛይቱም ሁለተኛውን ክፍል ስጡ፤” አለ። |
ደኅነኛውም ሕፃን የነበራት ሴት አንጀትዋ ስለ ልጅዋ ታውኳልና፥ “ጌታዬ ሆይ! አይደለም፤ ደኅነኛውን ለእርስዋ ስጣት እንጂ መግደልስ አትግደሉት” ብላ ለንጉሡ ተናገረች። ያችኛዪቱ ግን፥ “አካፍሉን እንጂ ለእኔም ለእርስዋም አይሁን” አለች።