ሁለተኛዪቱም ሴት፥ “አይደለም ደኅነኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው እንጂ አለች።” እንዲሁም በንጉሡ ፊት ይነጋገሩ ነበር።
1 ነገሥት 3:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜም ንጉሡ፥ “አንቺ፦ ደኅነኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞተውም የአንቺ ልጅ ነው ትያለሽ፤ አንቺም፦ አይደለም የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ ደኅነኛውም የእኔ ልጅ ነው ትያለሽ”። አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “ይህችኛዪቱ፣ ‘የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው፣ የአንቺ የሞተው ነው’ ትላለች፤ ያችኛዪቱ ደግሞ፣ ‘አይደለም የአንቺ ልጅ ሞቷል፣ በሕይወት ያለው የእኔ ነው’ ትላለች” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን “አንደኛዋ ‘በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!’ ትላለች፤ ሌላይቱ ደግሞ ‘አይደለም! የአንቺ ልጅ ሞቷል፤ የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው!’ ትላታለች አለ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን “አንደኛዋ ‘በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!’ ትላለች፤ ሌላይቱ ደግሞ ‘አይደለም! የአንቺ ልጅ ሞቶአል፤ የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው!’ ትላታለች አለ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ንጉሡ “ይህች ‘ደኅነኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞተውም የአንቺ ልጅ ነው፤’ ትላለች፤ ያችኛይቱም ‘አይደለም፤ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ ደኅነኛውም የእኔ ልጅ ነው፤’ ትላለች፤” አለ። |
ሁለተኛዪቱም ሴት፥ “አይደለም ደኅነኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው እንጂ አለች።” እንዲሁም በንጉሡ ፊት ይነጋገሩ ነበር።
የጻድቃን ልብ ታማኝነትን ይማራል፤ የኃአጥኣን አፍ ግን ክፋትን ይመልሳል። የደጋግ ሰዎች መንገዶች በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደዱ ናቸው፥ ስለ እነርሱም ጠላቶች ወዳጆችን ይሆናሉ።