La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 3:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሴት፥ “አይ​ደ​ለም ደኅ​ነ​ኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞ​ተው የአ​ንቺ ልጅ ነው እንጂ አለች።” እን​ዲ​ሁም በን​ጉሡ ፊት ይነ​ጋ​ገሩ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሌላዪቱም ሴት፣ “ነገሩ አንቺ እንደምትዪው አይደለም፤ የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለውም የእኔ ነው” አለች። የመጀመሪያዋ ሴት ግን አጠንክራ፣ “አይደለም! የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው” አለች፤ በዚህ ሁኔታም በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሁለተኛይቱ ሴት ግን፥ “አይደለም! በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!” አለች። የመጀመሪያይቱ ሴት “አይደለም! የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው!” አለች። በዚህም ዓይነት በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሁለተኛይቱ ሴት ግን፥ “አይደለም! በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!” አለች። የመጀመሪያይቱ ሴት “አይደለም! የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው!” አለች። በዚህም ዐይነት በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁለተኛይቱም ሴት “ደኅነኛው የኔ ልጅ ነው፤ የሞተውም የአንቺ ልጅ ነው እንጂ አንቺ እንደምትዪው አይደለም፤” አለች። ይህችም “የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ ደኅነኛውም የእኔ ልጅ ነው፤” አለች፤ እንዲሁም በንጉሡ ፊት ይነጋገሩ ነበር።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 3:22
2 Referencias Cruzadas  

ልጄ​ንም አጠባ ዘንድ በማ​ለዳ ብነሣ፥ ያን የሞ​ተ​ውን ልጅ አገ​ኘሁ፤ ነገር ግን ብር​ሃን በሆነ ጊዜ ተመ​ለ​ከ​ት​ሁት፤ እነ​ሆም፥ የወ​ለ​ድ​ሁት ልጄ አል​ነ​በ​ረም።”