እኔም በወለድሁ በሦስተኛው ቀን ይህች ሴት ወለደች፤ እኛ በቤት ውስጥ አብረን ነበርን፤ ከሁለታችንም በቀር ማንም በቤት ውስጥ አልነበረም።
1 ነገሥት 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም በላዩ ስለ ተኛችበት የዚህች ሴት ልጅ በሌሊት ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የዚህች ሴት ሕፃን ልጅ ስለ ተኛችበት ሌሊት ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዕለታት አንድ ቀን ሌሊት በላዩ ላይ ተኝታበት ስለ ታፈነ ልጇ ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕለታት አንድ ቀን ሌሊት በላዩ ላይ ተኝታበት ስለ ታፈነ ልጁ ሞተ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በላዩ ስለ ተኛችበት የዚህች ሴት ልጅ በሌሊት ሞተ። |
እኔም በወለድሁ በሦስተኛው ቀን ይህች ሴት ወለደች፤ እኛ በቤት ውስጥ አብረን ነበርን፤ ከሁለታችንም በቀር ማንም በቤት ውስጥ አልነበረም።
እርስዋም በእኩለ ሌሊት ተነሥታ፥ እኔ አገልጋይህ ተኝቼ ሳለሁ፥ ልጄን ከብብቴ ወሰደች፤ በብብቷም አስተኛችው፤ የሞተውንም ልጅዋን በእኔ ብብት አስተኛችው።