1 ነገሥት 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም በወለድሁ በሦስተኛው ቀን ይህች ሴት ወለደች፤ እኛ በቤት ውስጥ አብረን ነበርን፤ ከሁለታችንም በቀር ማንም በቤት ውስጥ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ከወለድሁ ከሦስት ቀን በኋላም፣ ይህች ሴት ወለደች፤ የነበርነው እኛ ብቻ ነን፤ ከሁለታችን በቀር በዚያ ቤት ማንም አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ በወለድኩ በሦስተኛው ቀን እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች፤ በዚያ ቤት ውስጥ ከሁለታችን በቀር ሌላ ማንም አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በወለድኩ በሦስተኛው ቀን እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደች፤ በዚያ ቤት ውስጥ ከሁለታችን በቀር ሌላ ማንም አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ከወለድሁ ከሦስት ቀን በኋላ ይህች ሴት ደግሞ ወለደች፤ እኛ በቤት ውስጥ አብረን ነበርን፤ ከሁለታችንም በቀር ማንም በቤት ውስጥ አልነበረም። |