እግዚአብሔርም አለው፥ “ፍርድን ትለይ ዘንድ ለራስህ ማስተዋልን ለመንህ እንጂ ለራስህ ብዙ ዘመናትን፥ ባለጠግነትንም፥ የጠላቶችህንም ነፍስ ሳትለምን ይህን ነገር ለምነሃልና፥
1 ነገሥት 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን ይህን በመለመኑ ጌታ ደስ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞን ይህን በመጠየቁ ጌታን ደስ አሰኘው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ይህን በመጠየቁ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፤ ነገሩ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው። |
እግዚአብሔርም አለው፥ “ፍርድን ትለይ ዘንድ ለራስህ ማስተዋልን ለመንህ እንጂ ለራስህ ብዙ ዘመናትን፥ ባለጠግነትንም፥ የጠላቶችህንም ነፍስ ሳትለምን ይህን ነገር ለምነሃልና፥
ስለዚህም ሰምቶ በሕዝብህ ላይ መፍረድ ይችል ዘንድ፥ መልካሙንና ክፉውንም ይለይ ዘንድ ለባሪያህ አስተዋይ ልቡና ስጠው፤ አለዚያማ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ዘንድ ማን ይችላል?”