እርሱም፥ “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥት ተመልሳ ለወንድሜ ሆናለች።
1 ነገሥት 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አንዲት ልመና እለምንሻለሁ ፤ ፊትሽንም አትመልሺብኝ” አላት። እርስዋም፥ “ተናገር” አለችው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም አንዲት ነገር እለምንሻለሁ፤ አታሳፍሪኝ” አላት። እርሷም፣ “በል ዕሺ ተናገር” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም የምጠይቅሽ አንድ ጉዳይ ስላለኝ እምቢ በማለት አታሳፍሪኝ።” ቤርሳቤህም “ጉዳይህ ምንድነው?” ስትል ጠየቀችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም የምጠይቅሽ አንድ ጉዳይ ስላለኝ እምቢ በማለት አታሳፍሪኝ።” ቤርሳቤህም “ጉዳይህ ምንድን ነው?” ስትል ጠየቀችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም አንዲት ልመና እለምንሻለሁ፤ አታሳፍሪኝ፤” አለ። እርስዋም “ተናገር፤” አለችው። |
እርሱም፥ “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥት ተመልሳ ለወንድሜ ሆናለች።
እርሱም፥ “ፊቱን አይመልስብሽምና፥ ሱነማዪቱን አቢሳን ይድርልኝ ዘንድ ለንጉሡ ለሰሎሞን እንድትነግሪው እለምንሻለሁ” አለ።
እርስዋም፥ “አንዲት ትንሽ ልመና እለምንሃለሁ፤ ፊትህን አትመልስብኝ” አለች። ንጉሡም፥ “እናቴ ሆይ! ፊቴን አልመልስብሽምና ለምኚ” አላት።