ድንጋዮችንም በእግዚአብሔር ስም መሠዊያ አድርጎ ሠራቸው፤ የፈረሰውንም መሠዊያ አደሰ፤ በመሠዊያውም ዙሪያ ሁለት መስፈሪያ እህል የሚይዝ ጕድጓድ ቈፈረ።
1 ነገሥት 18:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ። ደግሞም ጕድጓዱን በውኃ ሞላው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ፤ ጕድጓዱንም ሞላው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውሃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ፤ ጉድጓዱንም ሞላው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ፤ ጒድጓዱንም ሞላው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውሃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ፤ ደግሞም ጕድጓዱን ውሃ ሞላው። |
ድንጋዮችንም በእግዚአብሔር ስም መሠዊያ አድርጎ ሠራቸው፤ የፈረሰውንም መሠዊያ አደሰ፤ በመሠዊያውም ዙሪያ ሁለት መስፈሪያ እህል የሚይዝ ጕድጓድ ቈፈረ።
“አራት ጋን ውኃ አምጡልኝ፤ በሚቃጠለው መሥዋዕትና በእንጨቱ ላይም አፍስሱ” አለ፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ። ደግሞም፥ “ድገሙ” አለ፤ እነርሱም ደገሙ። እርሱም፥ “ሦስተኛ አድርጉ” አለ፤ ሦስተኛም አደረጉ።
ነቢዩ ኤልያስም ወደ ሰማይ አቅንቶ ጮኸ፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ፥ ስማኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ ዛሬ በእሳት ስማኝ፤ አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪያህ እንደ ሆንሁ፤ ይህንም ሥራ ስለ አንተ እንዳደረግሁ እነዚህ ሕዝቦች ይወቁ።
እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ፥ አፈሩንም ላሰች።