ከእርሱም ጋር ያደጉት፥ በፊቱ የሚቆሙት ብላቴኖች እንዲህ አሉት፥ “አባትህ ቀንበር አክብዶብናል፥ አንተ ግን ዛሬ አቃልልልን ለሚሉህ ሕዝብ፦ ታናሺቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች።
1 ነገሥት 12:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቃልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድን ነው?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አላቸው፤ “ ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች የምትሰጡኝ ምክር ምንድን ነው? ምንስ ብለን እንመልስላቸው?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ላደርገው ስለሚገባኝ ነገር ምን ትመክሩኛላችሁ? የአገዛዝ ቀንበር እንዳቀልላቸው ለጠየቁኝስ ሰዎች ምን መልስ ልስጣቸው?” ሲል ጠየቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ላደርገው ስለሚገባኝ ነገር ምን ትመክሩኛላችሁ? የአገዛዝ ቀንበር እንዳቀልላቸው ለጠየቁኝስ ሰዎች ምን መልስ ልስጣቸው?” ሲል ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቃልልልን፤’ ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው?” አላቸው። |
ከእርሱም ጋር ያደጉት፥ በፊቱ የሚቆሙት ብላቴኖች እንዲህ አሉት፥ “አባትህ ቀንበር አክብዶብናል፥ አንተ ግን ዛሬ አቃልልልን ለሚሉህ ሕዝብ፦ ታናሺቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች።
እርሱም፥ “አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድን ነው?” አላቸው።