La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 12:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም፥ “ለዚህ ሕዝብ አሁን አገ​ል​ጋይ ብት​ሆን፥ ብት​ገ​ዛ​ላ​ቸ​ውም፥ መል​ሰ​ህም በገ​ር​ነት ብት​ነ​ግ​ራ​ቸው፥ በዘ​መኑ ሁሉ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ይሆ​ኑ​ል​ሃል” ብለው ተና​ገ​ሩት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም፣ “ዛሬ አንተ ለዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆን፣ ብትገዛለትና ደስ የሚያሰኝ መልስ ብትሰጠው፣ ምን ጊዜም አገልጋይህ ይሆናል” ብለው መለሱለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሽማግሌዎቹም “ዛሬ ለእነዚህ ሰዎች ታዛዥ ሆነህ ብታገለግላቸውና ለጥያቄአቸውም ተስማሚ የሆነ መልስ ብትሰጣቸው፥ እነርሱም ዘወትር በታማኝነት ያገለግሉሃል” ሲሉ መለሱለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሽማግሌዎቹም “ዛሬ ለእነዚህ ሰዎች ታዛዥ ሆነህ ብታገለግላቸውና ለጥያቄአቸውም ተስማሚ የሆነ መልስ ብትሰጣቸው፥ እነርሱም ዘወትር በታማኝነት ያገለግሉሃል” ሲሉ መለሱለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም “ለዚህ ሕዝብ አሁን ባሪያ ብትሆን ብትገዛላቸውም፥ መልሰህም በገርነት ብትናገራቸው፥ በዘመኑ ሁሉ ባሪያዎች ይሆኑልሃል፤” ብለው ተናገሩት።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 12:7
9 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ትቶ ለሕ​ዝቡ ጽኑ ምላሽ መለ​ሰ​ላ​ቸው።


እርሱ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ትቶ ከእ​ርሱ ጋር ካደ​ጉ​ትና በፊቱ ይቆሙ ከነ​በ​ሩት ብላ​ቴ​ኖች ጋር ተማ​ከረ።


ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል።


ትዕ​ግ​ሥት ታላ​ቁን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና የገዢ ቍጣ የተ​ነ​ሣ​ብህ እንደ ሆነ ስፍ​ራ​ህን አት​ል​ቀቅ።


እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።