ንጉሡም፥ “በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመለሱ” ብሎ እንደ ተናገረ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ።
1 ነገሥት 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ሂዱ፥ በሦስተኛውም ቀን ወደ እኔ ተመለሱ” አላቸው። ሕዝቡም ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሮብዓምም፣ “ሂዱ፤ ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ” አላቸው። ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሮብዓምም “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” አላቸው፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሮብዓምም “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” አላቸው፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ሂዱ፤ በሦስተኛውም ቀን ወደ እኔ ተመለሱ፤” አላቸው። ሕዝቡም ሄዱ። |
ንጉሡም፥ “በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመለሱ” ብሎ እንደ ተናገረ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ።
ንጉሡም ሮብዓም፥ “ለዚህ ሕዝብ እመልስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድን ነው?” ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ።