1 ዮሐንስ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፣ እኛም እርስ በእርሳችን መዋደድ ይገባናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፥ እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ይህን ያኽል ካፈቀረን እኛም እርስ በርሳችን መፋቀር ይገባናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። |
“እርስ በርሳችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
ባልንጀሮቻችሁን ታገሡአቸው፤ እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ፤ ባልንጀሮቻችሁን የነቀፋችሁበትን ሥራ ተዉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እንዲሁ አድርጉ።
ወንድሞች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረቻችሁ አሮጌ ትእዛዝ እንጂ የምጽፍላችሁ አዲስ ትእዛዝ አይደለችም፤ አሮጌይቱ ትእዛዝ የሰማችኋት ቃል ናት።
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።
አሁንም እመቤት ሆይ! እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም።