እኔም ጠየቅሁት፤ እንዲህም አልሁት፥ “በፊትህ እናገር ዘንድ መንገድ ሰጥተኸኛልና እነሆ፥ በእውነት አንተ አልኸኝ፤ ወጣት የነበረች እናታችሁ ፈጽማ አረጀች፤ ኀይላችንስ እንደ ቀደሙን ሰዎች ኀይል ለምን አልሆነልንም?”