ያንጊዜ ይህን ሁሉ ከጻፈ በኋላ ዕዝራን ይዘው እንደ እርሱ ያሉ ሰዎች ወዳሉበት ሀገር ወሰዱት፤ እርሱም እስከ ዘለዓለም ድረስ የልዑል የጥበቡ ጸሓፊ ተባለ። የዕዝራ መጽሐፍ ተፈጸመ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባው፤ ለዘለዓለሙ አሜን።