1 ቆሮንቶስ 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመሄድ ቢቻለኝ ግን እኔ ራሴ እሄዳለሁና፥ እነርሱም አብረውኝ ይሄዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእኔ መሄድ የሚያስፈልግ ከሆነ ዐብረውኝ ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእኔ መሄድ የሚያስፈልግ ከሆነ አብረውኝ ይሄዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔም መሄድ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፤ አብረውኝ ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ደግሞ ልሄድ የሚገባኝ ብሆን ከእኔ ጋር አብረው ይሄዳሉ። |
በመጣሁ ጊዜም ስጦታችሁን ወደ ኢየሩሳሌም ያደርሱ ዘንድ የመረጣችኋቸውን ሰዎች መልእክቴን ጨምሬ እልካቸዋለሁ።
ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግልባት በዚች ጸጋ ከእኛ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ በአብያተ ክርስቲያናት ተሾመ።