1 ቆሮንቶስ 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ መንፈሴንና መንፈሳችሁን ደስ አሰኝተዋል፤ እንዲህ ያሉትንም ዕወቋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእኔንም የእናንተንም መንፈስ አሳርፈዋልና። ስለዚህ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች መታወቅ ይገባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእኔንም የእናንተንም መንፈስ አሳርፈዋታልና። እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እውቅና ይገባቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የእኔን መንፈስና የእናንተንም መንፈስ አሳርፈዋል፤ ስለዚህ እንደእነዚህ ያሉትን ሰዎች ዕወቁአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ እንደነዚህ ያሉትን እወቁአቸው። |
ስለዚህም ተጽናንተናል፤ በመጽናናታችንም ስለ ቲቶ ደስታ አብልጦ ደስ አለን፤ በሁላችሁ ዘንድ ሰውነቱን አሳርፋችኋታልና።
ወንድሞች ሆይ! በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ።
የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን መምህሮቻችሁን ዐስቡ፤ መልካም ጠባያቸውን አይታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው።