1 ቆሮንቶስ 14:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚተረጕም ከሌለ ግን በቤተ ክርስቲያን በቋንቋ የሚናገረው ዝም ይበል፤ በእግዚአብሔር መካከልና በእርሱ መካከል ይናገር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚተረጕም ሰው ከሌለ ግን በጉባኤ መካከል ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚተረጉም ሰው ከሌለ ግን፥ በጉባኤ መካከል ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚተረጒም ሰው ከሌለ ግን በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩት በስብሰባ ላይ ዝም ይበሉ፤ ለራሳቸውና ለእግዚአብሔር ብቻ ይናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚተረጉም ባይኖር ግን በማኅበር መካከል ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር። |