አንተም የጥበብ መንፈስ ለሞላሁባቸው፥ በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ተናገር። እነርሱም ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ ለአሮን ለቤተ መቅደስ የሚሆን የተለየ ልብስ ይሥሩ፤
1 ቆሮንቶስ 12:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሁሉም ጌታ እየረዳ በየዕድሉ እንደሚገባውና እንደሚጠቅመው ለእያንዳንዱ በግልጥ ይሰጠዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሰጠው ለጋራ ጥቅም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእያንዳንዱ የመንፈስን መገለጥ የሚሰጠው ለጥቅም ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእያንዳንዱ መንፈስ ቅዱስን የመግለጥ ስጦታ የሚሰጠው ለጋራ ጥቅም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል። |
አንተም የጥበብ መንፈስ ለሞላሁባቸው፥ በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ተናገር። እነርሱም ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ ለአሮን ለቤተ መቅደስ የሚሆን የተለየ ልብስ ይሥሩ፤
አካል አንድ እንደ ሆነ ብዙ የአካል ክፍሎችም እንደ አሉበት፥ ነገር ግን የአካል ክፍሎች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤
ነገር ግን ሌሎችን አስተምር ዘንድ፥ በቋንቋ ከሚነገር ብዙ ቃል ይልቅ በቤተ ክርስቲያን በአእምሮዬ አምስት ቃላትን ልናገር እሻለሁ።
ሁላችሁም በቋንቋ ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ይልቁንም ትንቢት ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ሳይተረጕም በቋንቋ ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር እጅግ ይበልጣልና፤ ቢተረጕም ግን ማኅበሩን ያንጻል።