ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥ ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል።
1 ቆሮንቶስ 12:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሁሉስ የመፈወስ ሀብት ይሰጣልን? ሁሉስ በቋንቋ ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጕማሉን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉስ የመፈወስ ስጦታዎች አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጕማሉን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጉማሉን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉም በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ችሎታ አላቸውን? ሁሉም በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የመተርጐም ችሎታ አላቸውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጉማሉን? |
ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥ ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል።
እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሾማቸው አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም መምህራንን፥ ከዚህም በኋላ ተአምራትና ኀይል ማድረግ የተሰጣቸውን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመርዳትም ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመምራትና ቋንቋን የመናገር ሀብት የተሰጣቸውን ነው።
በውኑ ሁሉ ሐዋርያትን ይሆናሉን? ሁሉስ ነቢያትን ይሆናሉን? ሁሉስ መምህራንን ይሆናሉን? ለሁሉስ ተአምራትን የማድረግ ኀይል ይሰጣልን?