1 ዜና መዋዕል 12:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የግዶር ሰው የይሮሐም ልጆች ዮዔላ፥ ዝባድያ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌዶር ሰው ከሆነው ደግሞ የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዝባድያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌዶር ሰው የይሮሐም ልጆች ዮዔላ፥ ዝባድያ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌዶር ሰው የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዝባድያ። |
ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ባለችው በአንባዪቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነዚህ ጋሻና ጦር የሚይዙ፥ ጽኑዓን፥ ኀያላን ሰልፈኞች፥ ወደ እርሱ ተጠጉ፤ ፊታቸውም እንደ አንበሳ ፊት ነበረ፤ በተራራም ላይ እንደሚዘልል ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ።
ሚስቱ አይሂዳም የጌዶርን አባት ያሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህ ሞሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።