እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ስለዚች አገልጋይህና ስለ ሕፃኑ አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና።
1 ዜና መዋዕል 1:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአብርሃምም ልጆች፤ ይስሐቅ፥ ይስማኤል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአብርሃም ወንዶች ልጆች፤ ይሥሐቅ፣ እስማኤል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአብርሃምም ልጆች፤ ይስሐቅና እስማኤል ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም ይስሐቅንና እስማኤልን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአብርሃምም ልጆች ይስሐቅ እና እስማኤል ናቸው። |
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ስለዚች አገልጋይህና ስለ ሕፃኑ አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና።