የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ሊቀበልህ በመምጣት ላይ ነው፤ አራት መቶ ሰዎችም ዐብረውት አሉ” አሉት።
ሩት 2:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞዓባዊቷ ሩትም ኑኃሚንን፣ “በፊቱ ሞገስ አግኝቼ ቃርሚያ የሚያስቃርመኝ ሰው ባገኝ እስኪ ወደ እህል አዝመራው ልሂድ” አለቻት። ኑኃሚንም፣ “ልጄ ሆይ፤ ይሁን ሂጂ” አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞአባዊቱም ሩት ናዖሚንን፦ “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው ተከትዬ እህል ለመቃረም ወደ እርሻ ልሂድ” አለቻት። እርሷም፦ “ልጄ ሆይ፥ ሂጂ” አለቻት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ሞአባዊትዋ ሩት ናዖሚን “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው እርሻ ሄጄ ቃርሚያ ልቃርም” አለቻት። ናዖሚም “ልጄ ሆይ! ሂጂ!” አለቻት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን “በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ፤” አለቻት። እርስዋም “ልጄ ሆይ! ሂጂ፤” አለቻት። |
የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ሊቀበልህ በመምጣት ላይ ነው፤ አራት መቶ ሰዎችም ዐብረውት አሉ” አሉት።
“ ‘የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ፣ የዕርሻችሁን ዳርና ዳር አትጨዱ፤ ቃርሚያውን አትልቀሙ፤ እነዚህንም ለድኾችና ለእንግዶች ተዉላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”
ስለዚህ እርሷም ወጣች፤ ከዐጫጆች ኋላ ኋላ እየተከታተለችም ከአዝመራው ቦታ ትቃርም ጀመር፤ እንዳጋጣሚ ትቃርምበት የነበረው አዝመራ ከአሊሜሌክ ጐሣ የሆነው የቦዔዝ ነበር።
እርሷም፣ ‘ዐጫጆቹን እየተከተልሁ በነዶው መካከል እንድቃርም እባክህ ፍቀድልኝ’ አለችኝ። ለጥቂት ጊዜ በመጠለያው ከማረፏ በቀር፣ ወደ አዝመራው ቦታ ገብታ ከጧት አንሥቶ እስካሁን ያለ ማቋረጥ ስትቃርም ቈይታለች።”