La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሩት 2:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ሩት እስኪመሽ ድረስ ከአዝመራው ላይ ቃረመች፤ ከዚያም የሰበሰበችውን ገብስ ወቃች፤ አንድ የኢፍ መስፈሪያም ያህል ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፥ የቃረመችውንም ወቃችው፥ ዐሥር ኪሎ ያህልም ገብስ ሆነ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሩትም እስከ ምሽት ድረስ ከእርሻው እህል ስትቃርም ዋለች፤ ባሸችውም ጊዜ ዐሥር ኪሎ ያኽል ሆነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፣ የቃረመችውንም ወቃችው፣ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህልም ገብስ ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፤ የቃረመችውንም ወቃችው፤ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህልም ገብስ ሆነ።

Ver Capítulo



ሩት 2:17
5 Referencias Cruzadas  

አንድ ጎሞር የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ ነው።


የቤተ ሰቦቿን ጕዳይ በትጋት ትከታተላለች፤ የስንፍና እንጀራ አትበላም።


ይልቁንም ከየታሰረው ነዶ ላይ ጥቂት ጥቂቱን ዘለላ እየመዘዛችሁ በመጣል እንድታነሣው ተዉላት፤ አታስቀይሟት።”


ያንም ይዛ ወደ ከተማ ሄደች፤ ዐማቷም የሰበሰበችው ምን ያህል እንደ ሆነም አየች፤ እንዲሁም ሩት የሚበቃትን ያህል ከበላች በኋላ አስተርፋ የነበረውን አውጥታ ለርሷ ሰጠቻት።