ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው፤ ይሥሐቅ የያዕቆብን ልብስ ካሸተተ በኋላ እንዲህ ብሎ መረቀው፤ “እነሆ፤ የልጄ ጠረን፣ እግዚአብሔር እንደ ባረከው፣ እንደ መስክ መዐዛ ነው።
ሩት 1:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዳችሁ በምታገቡት ባል ቤት እግዚአብሔር ያሳርፋችሁ።” ከዚያም ሳመቻቸው፤ እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በየባላችሁ ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ” አለቻቸው። ሳመቻቸውም፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዳችሁ እንደገና ባል አግብታችሁ ትዳር እንድትመሠርቱ እግዚአብሔር ይርዳችሁ።” ከዚህ በኋላ ናዖሚ ለመሰናበት ሳመቻቸው፤ እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በየባላችሁ ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ አለቻቸው። ሳመቻቸውም፣ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በየባላችሁ ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ፤” አለቻቸው። ሳመቻቸውም፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ። |
ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው፤ ይሥሐቅ የያዕቆብን ልብስ ካሸተተ በኋላ እንዲህ ብሎ መረቀው፤ “እነሆ፤ የልጄ ጠረን፣ እግዚአብሔር እንደ ባረከው፣ እንደ መስክ መዐዛ ነው።
ከዚያም ኑኃሚን ሁለቱን ምራቶቿን እንዲህ አለቻቸው፤ “እያንዳንዳችሁ ወደ እናቶቻችሁ ቤት ተመለሱ፤ ለሞቱ ባሎቻችሁና ለእኔ በጎ ነገር እንዳደረጋችሁ፣ ለእናንተም እግዚአብሔር እንደዚሁ ያድርግላችሁ፤