መዝሙር 97:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሳት በፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትንም ጠላቶቹን ይፈጃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሳት እፊት እፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ያቃጥላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለያዕቆብ ይቅርታውን ለእስራኤልም ቤት እውነቱን አሰበ፤ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ፥ የአምላካችንን ማዳን እዩ። |
እኔም አየሁ፤ ስመለከትም፣ እነሆ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል መጣ፤ ይኸውም በታላቅ ብርሃን የተከበበ፣ መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበረ፤ የእሳቱም መኻል የጋለ ብረት ይመስል ነበር።
የእሳት ወንዝ፣ ከፊት ለፊቱ ፈልቆ ይፈስስ ነበር፤ ሺሕ ጊዜ ሺሖች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍ በፊቱ ቆመዋል፤ የፍርድ ጉባኤ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ።
“እነሆ፤ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ገለባ ይሆናሉ፤ ያ የሚመጣው ቀንም ያቃጥላቸዋል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አያስቀርላቸውም።