መዝሙር 94:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በሕዝቡ መካከል ያላችሁ ደነዞች፤ ልብ በሉ፤ እናንተ ሞኞች፤ ጥበበኞች የምትሆኑት መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝብ ደንቆሮች ሆይ፥ አስተውሉ፥ ሞኞችስ መቼ ጠቢብ ትሆናላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕዝብ መካከል እናንተ አላዋቂዎች ይህን አስተውሉ፤ እናንተ ሞኞች ሆይ! አስተዋዮች የምትሆኑት መቼ ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑትና እንዳስቈጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ። |
“እናንተ አላዋቂዎች፤ ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወድዱታላችሁ? ፌዘኞች በፌዝ ደስ የሚሰኙት፣ ሞኞችስ ዕውቀትን የሚጠሉት እስከ መቼ ነው?
ቀደም ሲል እኛ ራሳችን ማስተዋል የጐደለን፣ የማንታዘዝ፣ የተታለልን፣ ለተለያየ ምኞትና ምቾት ባሪያ ሆነን የተገዛን ነበርን፤ እየተጣላንና እርስ በርስ እየተጠላላን በክፋትና በምቀኛነት እንኖር ነበር።