መዝሙር 94:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መበለቲቱንና መጻተኛውን ገደሉ፤ የድኻ አደጉንም ነፍስ አጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መበለቲቱንና ስደተኛውን አረዱ፥ ወላጅ አልባውንም ገደሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና አባትና እናት የሌላቸውን ልጆች ይገድላሉ፤ በምድራችን የሚኖሩትንም መጻተኞች ያጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፤ በእርሱ በፈጠረን በእግዚአብሔር ፊት እናልቅስ፤ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ከጨቋኙ እጅ አድኑት፤ መጻተኛውን፣ ወላጅ የሌለውንና መበለቲቱን አትበድሉ፤ አትግፏቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።
“ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።