መዝሙር 83:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሳት ደንን እንደሚያጋይ፣ ነበልባልም ተራራን እንደሚያቃጥል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሳት ደንን እንደሚያጋይ፥ የእሳት ነበልባልም ተራራዎችን እንደሚያቃጥል |
ሰዎቹ እንደ ኀይለኛ ውሃ ጩኸት ቢያስገመግሙም፣ እርሱ ሲገሥጻቸው፣ በኰረብታ ላይ በነፋስ እንደሚበንን ትቢያ፣ በዐውሎ ነፋስ ፊት እንደሚበተን ገለባ ይበተናሉ።
ከቀድሞ ጀምሮ ቶፌት የተባለ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅቷል፤ ለንጉሡም ተበጅቷል፤ ማንደጃ ጕድጓዱም ሰፊና ጥልቅ ነው፤ በውስጡም ብዙ እሳትና ማገዶ አለ፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ፈሳሽ ድኝ ያቀጣጥለዋል።
እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾኽንና ኵርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነድዳል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።
“እነሆ፤ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ገለባ ይሆናሉ፤ ያ የሚመጣው ቀንም ያቃጥላቸዋል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አያስቀርላቸውም።