መዝሙር 76:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ይህም የሆነው አንተ የምድር ጐስቋሎችን ለማዳን፣ ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ነው። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፥ ምድር ፈራች ዝምም አለች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በምድር የተጨቈኑትን ሁሉ ለመቤዠት፥ ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ዓለም ጸጥ አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ይቅርታን ይረሳልን? በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን? |
ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
እናንተ የምድር ትሑታን ሁሉ፣ ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤ ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤ በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ትሰወሩ ይሆናል።
ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምን ጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን፤