La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 76:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድንኳኑ በሳሌም፣ ማደሪያውም በጽዮን ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፥ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቤቱን በሳሌም (ኢየሩሳሌም) አደረገ፤ በጽዮንም ተራራ ላይ ይኖራል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመ​ከ​ራዬ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለ​ግ​ሁት፤ እጆ​ቼም በሌ​ሊት በፊቱ ናቸው፥ ጠላ​ቶ​ቼም አል​ረ​ገ​ጡ​ኝም። ነፍሴ ግን ደስ​ታን አጣች።

Ver Capítulo



መዝሙር 76:2
9 Referencias Cruzadas  

የልዑል አምላክ ካህን የነበረው የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤


አሁን ግን ስሜ በዚያ እንዲሆን ኢየሩሳሌምን፣ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲገዛም ዳዊትን መርጫለሁ።’


በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤ በተቀደሰ ድንኳኑም ውስጥ ይሸሽገኛል፤ በዐለቱ ላይ ከፍ ያደርገኛል።


የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው፣ በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው፣ በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው።


በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል በግልጽ አውሩ፤


የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”


ማደሪያውን እንደ አትክልት ስፍራ ባዶ አደረገ፤ መሰብሰቢያ ስፍራውን አፈረሰ፤ እግዚአብሔር ጽዮንን፣ ዓመት በዓላቶቿንና ሰንበታቷን እንድትረሳ አደረጋት፤ በጽኑ ቍጣው፣ ንጉሡንና ካህኑን እጅግ ናቀ።