እግዚአብሔርም መልአክ ልኮ በአሦር ንጉሥ ሰፈር ተዋጊዎችን፣ መሪዎችንና የጦር መኰንኖችን እንዲያጠፋቸው አደረገ። ስለዚህ ንጉሡ በውርደት ወደ ገዛ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩ ቤተ ጣዖት እንደ ገባም፣ የገዛ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት።
መዝሙር 76:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የገዦችን መንፈስ ይሰብራል፤ በምድር ነገሥታትም ዘንድ የተፈራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ፥ በዙሪያው ያሉ ሁሉ ለሚያስፈራው እጅ መንሻን ያስገቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢተኞች የሆኑትን መሳፍንት ያዋርዳል፤ ታላላቅ ነገሥታትንም ያርበደብዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ በሥራህም እጫወታለሁ። |
እግዚአብሔርም መልአክ ልኮ በአሦር ንጉሥ ሰፈር ተዋጊዎችን፣ መሪዎችንና የጦር መኰንኖችን እንዲያጠፋቸው አደረገ። ስለዚህ ንጉሡ በውርደት ወደ ገዛ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩ ቤተ ጣዖት እንደ ገባም፣ የገዛ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት።
እነዚህ መሥዋዕቶች ለእግዚአብሔር ሰንበት ከምታቀርቡት፣ ከስጦታችሁ፣ ከስእለታችሁና ከበጎ ፈቃድ ስጦታችሁ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ስጦታዎች ናቸው።
“ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ ምሽጋቸው ተደምስሷል፤ ማንም እንዳያልፍባቸው፣ መንገዳቸውን ባድማ አደረግሁ፤ ከተሞቻቸው ተደምስሰዋል፤ አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም ከቶ አይገኝባቸውም።
በዚህ ጊዜ ከዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ያሉት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፣ በባሕሩም ዳርቻ ያሉ የከነዓናውያን ነገሥታት በሙሉ እግዚአብሔር ዮርዳኖስን እስክንሻገር ወንዙን በእስራኤላውያን ፊት እንዴት እንዳደረቀው በሰሙ ጊዜ፣ ልባቸው በፍርሀት ቀለጠ፤ እስራኤላውያንንም ለመቋቋም ድፍረት ዐጡ።
ከዚህ በኋላ የምድር ነገሥታትና ገዦች፣ የጦር መኰንኖች፣ ሀብታሞች፣ ብርቱዎች፣ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ፤