መዝሙር 66:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች በራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ፤ በእሳትና በውሃ መካከል ዐለፍን፤ የኋላ ኋላ ግን ወደ በረከት አመጣኸን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው በራሳችን ላይ እንዲረማመድ አደረግህ፥ በእሳትና በውኃ መካከል አለፍን፥ ወደ በረከትም አወጣኸን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችን በግፍ እንዲረግጡን አደረግህ፤ በእሳትና በጐርፍ መካከል አለፍን፤ አሁን ግን ብልጽግና ወደ መላበት ወደ ሰፊ ቦታ አመጣኸን። |
ባስጨነቁሽ፣ ‘በላይሽ ላይ እንድንሄድ ተነጠፊልን’ ባሉሽ እጅ ላይ አደርገዋለሁ፤ ጀርባሽን እንደ መሬት፣ እንደ መሸጋገሪያም መንገድ አደረግሽላቸው።”
ናቡከደነፆርም ወደሚነድደው የእቶን እሳት በር ቀረብ ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ፣ “እናንተ የልዑል አምላክ አገልጋዮች ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ፤ ኑ ውጡ! ወደዚህ ኑ!” አላቸው። ስለዚህ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብድናጎ ከእሳቱ ወጡ፤
“አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፤ አንተ በምድራዊ ሕይወትህ ዘመን መልካም ነገሮችን እንደ ተቀበልህ፣ አልዓዛርም ደግሞ ክፉ ነገሮችን እንደ ተቀበለ አስታውስ፤ አሁን ግን እርሱ እዚህ ሲጽናና፣ አንተ በሥቃይ ላይ ትገኛለህ።
የደቀ መዛሙርቱንም ልብ በማበረታታትና በእምነታቸው ጸንተው እንዲኖሩ በመምከር፣ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ማለፍ አለብን” አሏቸው።
በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።