መዝሙር 5:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እብሪተኞች በፊትህ መቆም አይችሉም፤ ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ ጠላህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፥ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢተኞች በፊትህ አይቆሙም፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ትጠላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐመፀኞችም በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ዐመፅ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ። |
“እናንተ አላዋቂዎች፤ ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወድዱታላችሁ? ፌዘኞች በፌዝ ደስ የሚሰኙት፣ ሞኞችስ ዕውቀትን የሚጠሉት እስከ መቼ ነው?
“በጌልገላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሣ፣ እኔ በዚያ ጠላኋቸው፤ ስለ ሠሩት ኀጢአት፣ ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህም አልወድዳቸውም፤ መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸው።
ዐይኖችህ ክፉውን እንዳያዩ እጅግ ንጹሓን ናቸው፤ አንተ በደልን መመልከት አትችልም፤ ታዲያ፣ አታላዮችን ለምን ትመለከታለህ? ክፉው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠውስ፣ ለምን ዝም ትላለህ?
“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤