መዝሙር 5:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ ስምህን የሚወድዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ ተከላካይ ሁንላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፥ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አስወግዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ ከለላ ሥር ያሉ ሁሉ ይደሰቱ፤ ለዘለዓለምም እልል ይበሉ የአንተን ስም የሚወዱትን ሁሉ በደስታም እንዲፈነድቁ ከልላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘለዓለሙ ደስ ይላቸዋል፥ በእነርሱም ታድራለህ። ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ። |
ፍትሕ ማግኘቴን የሚወድዱ፣ እልል ይበሉ፤ ሐሤትም ያድርጉ፤ ዘወትርም፣ “የባሪያው ሰላም ደስ የሚለው፣ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።
አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን፣ ሐሤት ያድርጉ፤ በአንተም ደስ ይበላቸው፤ ዘወትር የአንተን ማዳን የሚወድዱ፣ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወድዱም ተስፋ የተሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?
“ሰማይ ሆይ፤ በርሷ ላይ ሐሤት አድርግ! ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያትም ሐሤት አድርጉ! በእናንተ ላይ ባደረሰችው ነገር እግዚአብሔር ፈርዶባታልና።”
“እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤ አንተን የሚወድዱህ ግን፣ የንጋት ፀሓይ በኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።” ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።