La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 41:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንጀራዬን የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ ተረከዙን አነሣብኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ክፉ ነገር መጣበት፥ ከተኛበት ከእንግዲህ ወዲህ አይነሣም ይላሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንጀራዬን ከእኔ ጋር አብሮ የበላ ከልብ የምተማመንበት ወዳጄ እንኳ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶአል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ አም​ላኬ ነህ፤ ለምን ረሳ​ኸኝ? ጠላ​ቶቼ ሲያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ለምን ተው​ኸኝ? ለም​ንስ አዝኜ እመ​ለ​ሳ​ለሁ?” ጠላ​ቶቼ ሁሉ አጥ​ን​ቶ​ቼን እየ​ቀ​ለ​ጣ​ጠሙ ሰደ​ቡኝ።

Ver Capítulo



መዝሙር 41:9
13 Referencias Cruzadas  

አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ የሆነው የጊሎን ሰው አኪጦፌል ከአገሩ ከጊሎ ወደ እርሱ እንዲመጣ ላከበት፤ ስለዚህ ሤራው ጥንካሬ አገኘ፤ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቍጥር እየጨመረ መጣ።


“ወንድሞቼን ከእኔ አርቋል፤ ከሚያውቁኝም ተገለልሁ።


የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤ የምወድዳቸውም በላዬ ተነሡ፤


በዐይኔ ፊት፣ ምናምንቴ ነገር አላኖርም። የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ ከእኔም ጋራ አይጣበቅም።


“በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ።


ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ድንበር ይገፉሃል፤ ጓደኞችህ ያታልሉሃል፤ ያሸንፉህማል፤ እንጀራህን የበሉ ወጥመድ ይዘረጉብሃል፤ አንተ ግን አታውቀውም።


ባልንጀራህን አትመን፤ በጓደኛህም አትታመን፤ በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ።


እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋራ እጁን ከወጭቱ ውስጥ ያጠለቀው ነው፤


“ስለ ሁላችሁ መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኋቸውን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን፣ ‘እንጀራዬን የሚበላ ተረከዙን አነሣብኝ’ የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።


ይሹሩን ወፈረ፤ ረገጠ፤ ጠገበ፤ ሰውነቱ ደነደነ፤ ለሰለሰ፤ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ መጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀ።