መዝሙር 41:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊጠይቀኝ የሚመጣ ቢኖር፣ በልቡ ስድብ እያጠራቀመ፣ ከዐንገት በላይ ይናገራል፤ ወጥቶም ወሬ ይነዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦ መቼ ይሞታል ስሙስ መቼ ይሻራል? ይላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን ለመጐብኘት የሚመጡት ከልባቸው አይደለም፤ በእኔ ላይ መጥፎ ወሬ ይሰበስባሉ፤ በየቦታውም እየዞሩ ስሜን ያጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፤ ስለዚህ አቤቱ በዮርዳኖስ ምድር፥ በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስብሃለሁ። |
“በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ።
ልባቸው ወደ ክፋት ያዘነበለው ሁለቱ ነገሥታት፣ በአንድ ገበታ ዐብረው ይቀመጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ሐሰትን ይነጋገራሉ፤ ነገር ግን የተወሰነው ጊዜ ገና ስለ ሆነ አይከናወንላቸውም።
ብዙ ጊዜ በጕዞ ተንከራትቻለሁ፤ ደግሞም ለወንዝ ሙላት አደጋ፣ ለወንበዴዎች አደጋ፣ ለገዛ ወገኖቼ አደጋ፣ ለአሕዛብ አደጋ፣ ለከተማ አደጋ፣ ለገጠር አደጋ፣ ለባሕር አደጋ እንዲሁም ለሐሰተኞች ወንድሞች አደጋ ተጋልጬ ነበር።