ጠላቴ በላዬ ድል አላገኘምና፣ እንደ ወደድኸኝ በዚህ ዐወቅሁ።
አንተ ግን አቤቱ፥ ማረኝ፥ እመልስላቸውም ዘንድ አቁመኝ።
እኔን ድል በማድረጋቸው እንደ ተደሰቱ አይቀሩም፤ አንተም በእኔ ደስ እንደ ተሰኘህ ዐውቃለሁ።
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
በጥርሳቸው ከመዘንጠል የጠበቀን፣ እግዚአብሔር ይባረክ።
በዚህም ጠላቴ፣ “አሸነፍሁት” እንዳይል፣ ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ።
ነገር ግን እግዚአብሔር በሚፈሩት፣ በምሕረቱ በሚታመኑትም ይደሰታል።
አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፤ እባክህ አታሳፍረኝ፤ ጠላቶቼም አይዘባነኑብኝ።
ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን እግሮቼን ሰፊ ቦታ ላይ አቆምሃቸው።
በልባቸው፣ “ዕሠይ! ያሰብነው ተሳካ! ዋጥ አደረግነውም” አይበሉ።
የሚጠሉኝ አይተው ያፍሩ ዘንድ፣ የበጎነትህን ምልክት አሳየኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ረድተኸኛልና፤ አጽናንተኸኛልም።
ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርቡ፤ የድኻውን ነፍስ፣ ከክፉዎች እጅ ታድጓልና።
የገዦችና የባለሥልጣናትንም ማዕርግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ።