መዝሙር 26:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴን ከኀጢአተኞች ጋራ፣ ሕይወቴንም ከደም አፍሳሾች ጋራ አታስወግዳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደም አፍሳሾች ከሆኑ ኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን አትውሰድ፤ ሕይወቴንም አታጥፋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊትህን ከእኔ አትመልስ፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ አምላኪዬና መድኀኒቴ ሆይ፥ ቸል አትበለኝ። |
በዳዊት ዘመነ መንግሥት፣ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፣ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
“እነርሱም መልሰው፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ተርበህ ወይም ተጠምተህ፣ እንግዳ ሆነህ ወይም ታርዘህ፣ ታምመህ ወይም ታስረህ አይተን መቼ አልደረስንልህም’ ይሉታል።
ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፣ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፣ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል።