መዝሙር 25:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጅነቴን ኀጢአት፣ መተላለፌንም አታስብብኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣ እንደ ምሕረትህም መጠን አስበኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፥ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! እንደ ቸርነትህ በዘለዓለማዊ ፍቅርህ አስበኝ እንጂ የወጣትነት ኃጢአቴን ወይም በደሌን አታስብብኝ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምስጋናህን ቃል እሰማ ዘንድ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ። |
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከልክ በላይ አትቈጣን፤ ኀጢአታችንንም ለዘላለም አታስብ፤ እባክህ ተለመነን፤ ፊትህን ወደ እኛ መልስ፤ ሁላችንም የአንተ ሕዝብ ነንና።
እንግዲህ ዕፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ ውርደታችንም ይሸፍነን፤ እኛም አባቶቻችንም፣ እግዚአብሔር አምላካችንን በድለናልና፤ ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን አልታዘዝንም።”
ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤” ይላል እግዚአብሔር። “በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ያን ሰው በቤተ መቅደስ አግኝቶ፣ “እነሆ፣ ተፈውሰሃል፤ ከእንግዲህ ግን ኀጢአት አትሥራ፤ አለዚያ ከዚህ የባሰ ይደርስብሃል” አለው።