በመላው የእስራኤል ነገዶችም፣ ሕዝቡ እንዲህ እያለ እርስ በርሱ ይከራከር ነበር፤ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ አውጥቶናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ የታደገን እርሱ ነው፤ አሁን ግን በአቤሴሎም ምክንያት ከአገር ሸሽቶ ሄዷል፤
መዝሙር 18:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕዝብ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤ የሕዝቦች መሪ አድርገህ አስቀመጥኸኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ትቢያ በነፋስ ፊት እፈጫቸዋለሁ፥ እንደ አደባባይም ጭቃ እረግጣቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዐመፀኛ ሕዝብ አዳንከኝ፤ በአሕዛብም ላይ ሾምከኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ይገዛልኛል። |
በመላው የእስራኤል ነገዶችም፣ ሕዝቡ እንዲህ እያለ እርስ በርሱ ይከራከር ነበር፤ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ አውጥቶናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ የታደገን እርሱ ነው፤ አሁን ግን በአቤሴሎም ምክንያት ከአገር ሸሽቶ ሄዷል፤
እርሱም፣ “ባሪያዬ መሆንህ፣ የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣ የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤ ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።
እነሆ፤ የማታውቃቸውን መንግሥታት ትጠራለህ፤ የማያወቁህ መንግሥታት በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ በክብሩ ከፍ ከፍ አድርጎሃል።”
“ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ሊሰፈርና ሊቈጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናሉ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ በተባሉበት ቦታ፣ ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።
ቀድሞ የርሱ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆናችኋል፤ ቀድሞ ምሕረትን አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፤ “የዓለም መንግሥት፣ የጌታችንና የርሱ ክርስቶስ መንግሥት ሆነች፤ እርሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”