መዝሙር 18:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከሰማይ አንጐደጐደ፤ ልዑል እግዚአብሔር ድምፁን አሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከልዩ ሰው ባሪያህን አድነው። ካልገዙኝ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኀጢአቴ እነጻለሁ። |
የሚያጠፋ ራብ፣ በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድድባቸዋለሁ፤ የአራዊትን ሹል ጥርስ፣ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድድባቸዋለሁ።
ከቤትሖሮን ወደ ዓዜቃ ቍልቍል በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሸሹበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ በእስራኤላውያን ሰይፍ ካለቁት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋይ ያለቁት በልጠው ተገኙ።
ደግሞም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ኀይለኛ ወራጅ ውሃ ድምፅ፣ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ የሚመስል እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን ቻይ ጌታ አምላካችን ነግሧልና።
ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ይሁን እንጂ በዚያ ዕለት እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ ስላንጐዳጐደባቸው እጅግ ተሸበሩ፤ ድልም ተመተው ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ።