መዝሙር 141:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዐመፀኞች ጋራ፣ በክፉ ሥራ እንዳልተባበር፣ ልቤን ወደ ክፉ አታዘንብል፤ ከድግሳቸውም አልቋደስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፅን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለክፋት ምክንያት እንዳልሰጥ፥ ከድግሳቸውም አልቅመስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስሕተት ለማድረግ ከመመኘትና ከክፉ አድራጊዎች ጋር በክፉ ሥራ ከመተባበር ጠብቀኝ፤ የበዓላቸው ግብዣ ተካፋይ ከመሆን ጠብቀኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቀኝም ተመልሼ አየሁ፥ የሚያውቀኝም አጣሁ፤ መሸሸጊያም የለኝም፥ ስለ ሰውነቴም የሚመራመር የለም። |
የእግዚአብሔር ሰው ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ግማሽ ሀብትህን ብትሰጠኝ እንኳ፣ ዐብሬህ አልሄድም፤ እዚህ፣ እንጀራ አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም።
“እግዚአብሔርም፣ ‘እንዴት አድርገህ?’ ሲል ጠየቀው። “እርሱም፣ ‘እኔ እወጣና፤ በገዛ ነቢያቱ ሁሉ አፍ የሐሰት መንፈስ እሆናለሁ’ አለ። “እግዚአብሔርም፣ ‘ታሳስተዋለህ፤ ይሳካልሃልም፤ እንግዲህ ውጣና አድርግ’ አለው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከመንገድህ እንድንወጣ፣ ልባችንን በማደንደን ለምን እንዳንፈራህ አደረግኸን? ስለ ባሮችህ ስትል፣ ስለ ርስትህ ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።
ይሁን እንጂ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን እንድናልፍ አልፈቀደልንም፤ ምክንያቱም አምላካችሁ እግዚአብሔር አሁን እንዳደረገው ሁሉ እርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ለመስጠት መንፈሱን አደንድኖት፣ ልቡንም አጽንቶት ነበር።