መዝሙር 109:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ፤ ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተተኪ አይኑረው፥ በቀጣይ ትውልድ ስማቸው ይደምሰስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለስሙ መጠሪያ የሚሆን አንድ ልጅ እንኳ አይቅርለት፤ ከአንድ ትውልድ በኋላ የሚያስታውሰው አይኑር። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣ አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤ በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣ መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”
አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፣ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስስ፤ ከቶ እንዳትረሳ!
እግዚአብሔር ለዚያ ሰው ፈጽሞ ይቅርታ አያደርግለትም፤ ቍጣውና ቅናቱ በርሱ ላይ ይነድድበታል። በዚህ መጽሐፍ የተጻፈው ርግማን ሁሉ ይወርድበታል፤ እግዚአብሔርም ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል።
ዔሊ በሚያውቀው ኀጢአት ምክንያት በቤተ ሰቡ ላይ ለዘላለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር፤ ልጆቹ አስጸያፊ ነገር አድርገዋል፤ እርሱ ግን አልከለከላቸውም።