ያለውን ሁሉ ዕዳ ጠያቂ ይውረሰው፤ የድካሙንም ዋጋ ባዕዳን ይቀሙት።
ባለዕዳም ያለውን ሁሉ ይበርብረው፥ እንግዶችም ድካሙን ሁሉ ይበዝብዙት።
ንብረቱ ሁሉ በዕዳ ይያዝበት፤ ለፍቶ ያገኘውን ጥሪት ሁሉ ባዕዳን ሰዎች ይውሰዱበት።
የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤
ከእሾኽ መካከል እንኳ አውጥቶ፣ ራብተኛ ሰብሉን ይበላበታል፤ ጥማተኛም ሀብቱን ይመኝበታል።
በእኩለ ቀን፣ በጨለማ እንዳለ ዕውር በዳበሳ ትሄዳለህ። የምታደርገው ሁሉ አይሳካልህም። በየዕለቱ ትጨቈናለህ፤ ትመዘበራለህም፤ የሚታደግህ አይኖርም።