በእስራኤል ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዷ እኔ ነኝ፤ አንተ በእስራኤል እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት ትሻለህ፤ የእግዚአብሔርን ርስት ለመዋጥ የፈለግኸው ለምንድን ነው?”
መዝሙር 106:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም የምርጦችህን ብልጽግና አይ ዘንድ፣ በሕዝብህ ደስታ ደስ ይለኝ ዘንድ፣ ከርስትህም ክብር የተነሣ እጓደድ ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥ በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከርስትህም ጋር እኮራ ዘንድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ ከሚመኩት ወገኖችህ እንደ አንዱ ሆኜ፥ ሕዝቦችህ ሲበለጽጉ እንዳይና የወገኖችህንም ደስታ እንድካፈል አድርገኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራቡ፥ ተጠሙም፥ ሰውነታቸውም በላያቸው አለቀች። |
በእስራኤል ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዷ እኔ ነኝ፤ አንተ በእስራኤል እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት ትሻለህ፤ የእግዚአብሔርን ርስት ለመዋጥ የፈለግኸው ለምንድን ነው?”
እርሱም በወራጅ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ነው፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በወጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣ ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ።
እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
“ወዳጆቿ የሆናችሁ ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ስለ እርሷም ሐሤት አድርጉ፤ ለርሷ ያለቀሳችሁ ሁሉ፣ ከርሷ ጋራ እጅግ ደስ ይበላችሁ።
የጽዮን ሰዎች ሆይ፤ ደስ ይበላችሁ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ሐሤት አድርጉ፤ የበልግን ዝናብ፣ በጽድቅ ሰጥቷችኋልና፤ እንደ ቀድሞውም፣ የበልግንና የጸደይን ዝናብ በብዛት ልኮላችኋል።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።
እንዲሁም በርሱ የተጠራችሁለት ተስፋ፣ ይህም በቅዱሳኑ ዘንድ ያለውን ክቡር የሆነውን የርስቱን ባለጠግነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ
አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ስለ ሆንህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ፣ ርስትም እንድትሆንለት በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ መረጠህ።
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር እናንተን ከመጀመሪያ አንሥቶ በመንፈስ ተቀድሳችሁና በእውነትም አምናችሁ እንድትድኑ መርጧችኋል።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወድዱም ተስፋ የተሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?
እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉ ግን ድል ይነሣቸዋል፤ ምክንያቱም እርሱ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ ከርሱ ጋራ ያሉ የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ዐብረው ድል ይነሣሉ።”